የቴሌግራም (Telegram) አካውንታችንን ከጠላፊዎች እንዴት እንጠብቅ?
መግቢያ ቴሌግራም በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ተጠቃሚ ያለው መተግበሪያ ነው። ነገር ግን ብዙ ሰዎች የቴሌግራም አካውንታቸው እየተጠለፈ (Hack እየተደረገ) ለተለያዩ ችግሮች ሲጋለጡ ይስተዋላል። ዛሬ አካውንታችሁን አስተማማኝ ለማድረግ መከተል ያለባችሁ 3 ወሳኝ መንገዶችን እናያለን። 1. "Two-Step Verification" ማብራት ይህ በጣም አስፈላጊው የደህንነት መቆለፊያ ነው። ይህንን ካበራችሁ ማንም ሰው የእናንተን የኤስኤምኤስ (SMS) ኮድ ቢያገኝ እንኳ እናንተ የፈጠራችሁትን የይለፍ ቃል (Password) ካላወቀ ሊገባ አይችልም። እንዴት እንደሚበራ፦ Settings > Privacy and Security > Two-Step Verification > Set Password። 2. "Active Sessions" መቆጣጠር አካውንታችሁ በሌላ ሰው ስልክ ወይም ኮምፒውተር ላይ ተከፍቶ እንደሆነ ለማወቅ ይህንን ዘዴ ይጠቀሙ። የማታውቁት መሣሪያ ካለ ወዲያውኑ ማጥፋት ወይም ማስወጣት ትችላላችሁ። እንዴት እንደሚታይ፦ Settings > Devices የሚለው ውስጥ በመግባት የማታውቁትን መሣሪያ "Terminate" ያድርጉ። 3. የፕሮፋይል ፎቶ እና ስልክ ቁጥር መደበቅ ስልክ ቁጥራችሁን ማንም ሰው እንዳያየው ማድረግ አላስፈላጊ ለሆኑ ጥቃቶች እንዳትጋለጡ ይረዳል። ይህ ግን ቀላል የሚመስል በጣም ጠቃሚ ነገር ነዉ ። እንዴት እንደሚስተካከል፦ Privacy and Security > Phone Number > "Nobody" የሚለውን ይምረጡ። ማጠቃለያ ቴክኖሎጂን ስንጠቀም ደህንነታችንን መጠበቅ ቀዳሚ ተግባራችን መሆን አለበት። ...