በስልካችን ኢንተርኔት (Data) ቶሎ እንዳያልቅብን ምን እናድርግ
መግቢያ ሳላም! የTechmedrek ቤተሰብ ዛሬ አርብ ሜይ 15 ነው በአሁኑ ሰዓት በጣም ጠቃሚ የሆነ ርዕስ መርጫለሁ እስከ መጨረሻ ተከታተሉን ። የኢንተርኔት ዳታ ዋጋ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ የገዛነው ጥቅል ሳይታወቅ ቶሎ ማለቁ ትልቅ ችግር ነው። ነገር ግን ጥቂት ቅንብሮችን በማስተካከል ዳታችንን መቆጠብ እንችላለን። 1. አውቶማቲክ አፕዴት (Auto-update) ማቆም Play Store ውስጥ በመግባት Settings > Network Preferences > Auto-update apps የሚለውን "Over Wi-Fi only" ወይም "Don't auto-update" ማድረግ። ይህ ስልካችን እኛ ሳናውቅ ጥቅል እንዳይበላ ይረዳል። 2. ዳታ ሴቨር (Data Saver) ማብራት በስልካችን Settings > Connections > Data Usage ውስጥ በመግባት "Data Saver" የሚለውን ማብራት። ይህ ከጀርባ (Background) ዳታ የሚበሉ አፖችን ይገድባል። 3. የማህበራዊ ሚዲያ ቅንብሮች TikTok/YouTube: ቪዲዮዎች በጥራት (HD) ፋንታ "Data Saver" ሞድ ላይ እንዲሆኑ ማድረግ። Telegram/WhatsApp: ፎቶዎችና ቪዲዮዎች ያለ እኛ ፍቃድ (Auto-download) እንዳይወርዱ ማስተካከል። ማጠቃለያ እነዚህን ቀላል መንገዶች በመጠቀም የገዙትን ጥቅል ለረጅም ጊዜ መጠቀም ይችላሉ። ይህ መረጃ ለሌሎች እንዲደርስ ለጓደኞችዎ ያጋሩ።