በስልክዎ ውስጥ ያለውና ብዙዎች የማያውቁት አስገራሚው "Google Lens" እና 3 ጥቅሞቹ
መግቢያ በስልካችን ካሜራ ብቻ ነገሮችን መለየት፣ ጽሁፎችን መተርጎም እና የቤት ስራዎችን መስራት እንደምንችል ያውቃሉ? ጎግል ሌንስ (Google Lens) አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን እንድንረዳ የሚያደርግ ድንቅ መሣሪያ ነው። ዛሬ ሊያውቋቸው የሚገቡ 3 ዋና ዋና ጥቅሞቹን እናያለን። ብዙዎቻችን ይሄን ምስጥር አናውቅም በጣም ጠቃሚ ነገር ነዉ። 1. ማንኛውንም ጽሁፍ ከወረቀት ላይ ኮፒ (Copy) ለማድረግ በደብተር ወይም በወረቀት ላይ የተጻፈን ጽሁፍ መልሰው መተየብ አሰልቺ ነው? ጎግል ሌንስን በመክፈት ጽሁፉ ላይ ካሜራዎን ያዙሩ፤ ወዲያውኑ ጽሁፉን ወደ ዲጂታል ፎርማት ይቀይርላችኋል (Copy text)። ከዚያም ወደ ቴሌግራም ወይም ኢሜይል መውሰድ ትችላላችሁ። 2. የቋንቋ ትርጉም በካሜራ (Live Translation) የማታውቁት ቋንቋ የተጻፈበት ማስታወቂያ ወይም መመሪያ ካጋጠማችሁ፣ ጎግል ሌንስን ተጠቅማችሁ ካሜራችሁን ጽሁፉ ላይ ስታደርጉት፣ ወዲያውኑ ወደምትፈልጉት ቋንቋ (ለምሳሌ ወደ አማርኛ) ይተረጉምላችኋል። 3. ምርቶችን እና ቁሳቁሶችን መለየት አንድ ያያችሁት ጫማ፣ ልብስ ወይም የቤት ዕቃ ስሙን ካላወቃችሁት ወይም የት እንደሚሸጥ መፈለግ ከፈለጋችሁ፣ በጎግል ሌንስ ፎቶ በማንሳት ብቻ ተመሳሳይ ምርቶችንና ዋጋቸውን ማግኘት ትችላላችሁ። ዕፅዋትንና እንስሳትን ለመለየትም ያገለግላል። ይህን (google lens) በመጠቀም ብቻ ብዙ ጥቅሞችንና አገልግሎቶችን ማግኘት እንችላለን ማለት ነው። ማጠቃለያ ጎግል ሌንስ በሁሉም አንድሮይድ እና አይፎን ስልኮች ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የዕለት ተዕለት ሥራችንን በእጅጉ ያ...