ስለ ዋትስአፕ (WhatsApp) የማታውቋቸው 4 አስገራሚ ድብቅ ጥቅሞች
መግቢያ ሳላም የTechmedrek ቤተሰብ ዛሬ እስቲ ብዙዎቻቹ የማይታወቁት በጣም ጠቃሚ የሆነ የዋትስአፕ 4 አስገራሚ ድብቅ setting ልንገራችሁ ። ዋትስአፕን ለጽሁፍ መልዕክት መላላኪያ ብቻ ነው የምትጠቀሙበት? እንግዲያውስ ብዙ ጠቃሚ አገልግሎቶችን እያመለጣችሁ ነው። ዛሬ ዋትስአፕን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድትጠቀሙበት የሚረዱ 4 ድብቅ ዘዴዎችን እናሳያችኋለን። 1. ለራስዎ መልዕክት መላክ (Message Yourself) ይህ ዘዴ እንደ ማስታወሻ ደብተር ያገለግላል። ጠቃሚ ሊንኮችን፣ ፎቶዎችን ወይም የሥራ ዝርዝርዎን (To-do list) ለራስዎ በመላክ ሁልጊዜ ዝግጁ ማድረግ ይችላሉ። እንዴት? አዲስ ቻት ለመጀመር "Contacts" ውስጥ ሲገቡ ስምዎ መጀመሪያ ላይ ይመጣል። 2. የፎቶ ጥራትን ሳይቀንሱ መላክ (HD Quality) ብዙ ጊዜ ዋትስአፕ ላይ ፎቶ ስንልክ ጥራቱ ይቀንሳል። አሁን ግን ጥራቱን እንደጠበቀ መላክ ይቻላል። እንዴት? ፎቶውን መርጠው ከመላክዎ በፊት ከላይ ያለውን "HD" የሚለውን ምልክት ይጫኑ። 3. የደረሰንን ድምፅ (Voice Message) ሳንሰማ ወደ ጽሁፍ መቀየር ጫጫታ ባለበት ቦታ ከሆኑ ወይም ድምፅ ለመስማት ካልተመቸዎት፣ ዋትስአፕ አሁን ድምፁን ወደ ጽሁፍ የመቀየር (Transcribe) ችሎታ አለው። እንዴት? በሴቲንግ ውስጥ "Chats > Voice Message Transcripts" የሚለውን ያብሩት። 4. የላኩትን መልዕክት ማስተካከል (Edit Message) መልዕክት ልከው ስህተት ካገኙበት፣ መልዕክቱን አጥፍተው በድጋሚ መጻፍ አያስፈልግዎትም። እንዴ...