ልጥፎች

ልጥፎችን ከመለያ security ጋር በማሳየት ላይ

ስልክዎ ቢጠፋ ወይም ቢሰረቅ እንዴት ሊያገኙት ይችላሉ? (Find My Device)

ምስል
  ​ መግቢያ ሳላም የTechmdrek ቤተሰብ  ዛሬ ለስልካችንም ሆነ ለራሳችን  ደህነት በጣም  ጠቃሚ  የሆነ መረጃ ይዤ  መጥቻለሁ  መረጃቸውን  ከወደዱት ለወዳጆቹ share ማድረጉን እንዳይረሳ ። የስልካችን መጥፋት ትልቅ ራስ ምታት ነው። መረጃዎቻችን፣ ፎቶዎቻችን እና የባንክ መተግበሪያዎቻችን ሁሉ ስልካችን ላይ ስለሆኑ ደህንነቱ ያሳስበናል። ነገር ግን ስልካችን ሳይጠፋ በፊት ልናደርጋቸው የሚገቡ እና ከጠፋ በኋላ የምንጠቀምባቸው ቀላል መንገዶች አሉ። ​ 1. "Find My Device" ማብራት ይህ ጎግል ያዘጋጀው ድንቅ አገልግሎት ነው። ስልክዎ ሳይጠፋ በፊት Settings > Security > Find My Device የሚለውን ማብራትዎን ያረጋግጡ። ይህም ስልኩ የት እንዳለ በካርታ ላይ ለማየት ይረዳል። ​ 2. በሌላ ስልክ ወይም ኮምፒውተር መፈለግ ስልክዎ ከጠፋብዎ፣ በሌላ ስልክ ላይ ጎግል ላይ በመግባት "Find My Device" ብለው ይፈልጉ። በስልኩ ላይ ያለውን የጂሜይል (Gmail) አካውንትዎን በማስገባት የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦ ​ Play Sound፦ ስልኩ "Silent" ቢሆንም እንኳ ለ5 ደቂቃ ድምፅ እንዲያሰማ ማድረግ። ​ Secure Device፦ ስልኩን "Lock" ማድረግና ስክሪኑ ላይ የእርስዎን ሌላ ስልክ ቁጥር እንዲያሳይ ማድረግ። ​ Erase Device፦ ስልኩ የሚገኝ ካልሆነ መረጃዎችዎ ለሌላ ሰው እንዳይሳለፉ በሩቅ ሆነው ሁሉንም መረጃ ማጥፋት። ​ 3. የIMEI ቁጥርዎን መያዝ የእያንዳንዱ ስልክ መለያ ወይም IMEI ቁጥር ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። ስልክዎ ላይ * #06# በመደወል የሚመጣውን ቁጥር የሆነ ቦታ ላይ ጽፈው ያስቀምጡ። ስል...