ልጥፎች

ልጥፎችን ከመለያ (Tech tips)(mobile care) ጋር በማሳየት ላይ

ስልክዎ ከመጠን በላይ ይሞቃል? ምክንያቶቹ እና 5 መፍትሄዎች

ምስል
  ​ መግቢያ ስላም  የtech medrek ቤተሰብ የዛሬ  መረጃ በጣም  ቀላልና  ለስልካችን ግን እጅግ በጣም  ጠቃሚ  ነገር ነው። የስልካችን መሞቅ (Overheating) ባትሪውን ከማዳከሙም ባለፈ የስልኩን እድሜ ያሳጥረዋል። ስልካችን ለምን ይሞቃል? በቀላሉስ እንዴት ማቀዝቀዝ እንችላለን? ዛሬ መፍትሄዎቹን ይዘንላችሁ ቀርበናል። ​ 1. ከባድ መተግበሪያዎችን (Apps) ለረጅም ጊዜ መጠቀም ከፍተኛ ግራፊክስ ያላቸውን ጌሞች መጫወት ወይም ቪዲዮ ኤዲቲንግ አፖችን ለረጅም ሰዓት መጠቀም ፕሮሰሰሩ ላይ ጫና ስለሚፈጥር ስልኩ እንዲሞቅ ያደርጋል። አልፎ አልፎ ስልኩን ማሳረፍ ተገቢ ነው። ​ 2. ቻርጅ እያደረጉ ስልክ መጠቀም ስልክ ቻርጅ በሚደረግበት ወቅት ባትሪው ሙቀት ያመነጫል። በዚህ ሰዓት ተጨማሪ ስራዎችን (ለምሳሌ Game ቪዲዮ ማየት) መስራት ሙቀቱን በእጥፍ ይጨምረዋል። ይህ ለባትሪ ደህንነት አደገኛ ነው። ​ 3. አላስፈላጊ የሆኑ ኮኔክሽኖችን ማብራት ዋይፋይ (Wi-Fi)፣ ብሉቱዝ (Bluetooth) እና ጂፒኤስ (GPS) ባንፈልጋቸውም እንኳ ክፍት ሆነው ሲቀሩ ስልኩ ሲግናል ለመፈለግ በሚያደርገው ጥረት ሙቀት ይፈጥራል። ካልፈለግናቸው ብንዘጋቸው ይመከራል። ​ 4. የስልኩን ከቨር (Case) ለጥቂት ጊዜ ማውለቅ አንዳንድ ወፍራም የስልክ ከቨሮች ሙቀት ወደ ውጭ እንዳይወጣ ያደርጋሉ። ስልኩ በጣም መሞቅ ሲጀምር ከቨሩን በማውለቅ አየር እንዲያገኝ ወይም እንዲቀዘቅዝ ማድረግ ፍቱን መፍትሄ ነው። ​ 5. ሲስተም አፕዴት (System Update) ማድረግ አንዳንድ ጊዜ ስልኩ የሚሞቀው በሶፍትዌር ችግር ሊሆን ይችላል። የቅርብ ጊዜውን አፕዴት ማድረግ ወይም software ማሳደስ እነዚህን ችግሮች ሊቀርፍ ...