ልጥፎች

ልጥፎችን ከመለያ (የስልክ መረጃ)( ​Tech Tips)( ​ደህንነት) ጋር በማሳየት ላይ

ስልካችንን ስንገዛ Original (ዋናው) መሆኑን በ 2 ደቂቃ ውስጥ የምናረጋግጥበት ቀላሉ መንገድ

ምስል
  ​ መግቢያ  ሳላም የTechmedrek ቤተሰቦች በዛሬ መረጃችን አዲስም ሆነ ያገላገለ ስልክ ስንገዛ ማድረግ ያለብንን  ጥንቃቄዎች  እናያለን ። በአሁኑ ሰዓት በገበያ ላይ ኦሪጅናል የሚመስሉ ነገር ግን የፎርጅድ (Copy) ስልኮች በጣም በዝተዋል። ከፍተኛ ብር አውጥተን የገዛነው ስልክ ትክክለኛ መሆኑን እንዴት በቀላሉ ማወቅ እንችላለን? መልሱ እጅግ ቀላል ነው፤ የ IMEI ቁጥርን መጠቀም። ​ 1. የ IMEI ቁጥርን ማግኘት በማንኛውም ስልክ ላይ የስልክ መደወያውን በመክፈት *#06# ብለው ሲደውሉ ባለ 15 አሃዝ የ IMEI ቁጥር ይመጣልዎታል። ይህንን ቁጥር ስክሪንሹት ያድርጉት ወይም ወረቀት ላይ ይጻፉት። ​ 2. በ imei.info ድረ-ገጽ ማረጋገጥ የመቶ ዓመት ዕድሜ ባለው ስማርትፎንዎ ላይ ኢንተርኔት በመክፈት ወደ www.imei.info ድረ-ገጽ ይግቡ። የጻፉትን 15 አሃዝ ቁጥር እዚያ ላይ አስገብተው "Check" የሚለውን ይጫኑ። ​ 3. ውጤቱን ማወዳደር ድረ-ገጹ የስልኩን ትክክለኛ ሞዴል፣ የተመረተበትን ኩባንያ (Samsung, iPhone, Techno ወዘተ) እና ዝርዝር መረጃዎችን ያሳየዎታል። በእጅዎ ያለው ስልክ እና ድረ-ገጹ ላይ የመጣው መረጃ ፍጹም አንድ አይነት ካልሆነ ስልኩ ፎርጅድ ወይም የተቀየረ መሆኑን በቀላሉ ማወቅ ይችላሉ። ​ ማጠቃለያ አዲስም ሆነ ያገለገለ ስልክ ከመግዛትዎ በፊት ይህንን ቀላል ፍተሻ በማድረግ ራስዎን ከኪሳራ ይጠብቁ።