ልጥፎች

ልጥፎችን ከመለያ wiffi safety ጋር በማሳየት ላይ

የህዝብ ዋይፋይ (Public Wi-Fi) ሲጠቀሙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ 3 ወሳኝ ጥንቃቄዎች ​መግቢያ

ምስል
መግቢያ በሆቴሎች፣ በካፌዎች ወይም በኤርፖርቶች የምናገኘውን የህዝብ ዋይፋይ መጠቀም ቀላልና ነፃ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ዋይፋዮች ለጠላፊዎች (Hackers) በጣም ምቹ ናቸው። የግል መረጃዎቻችሁ፣ የባንክ መረጃ እና ፓስወርድ እንዳይሰረቅ ዛሬ የምንነግራችሁን 3 ጥንቃቄዎች ይተግብሩ። ​ 1. የባንክ እና የገንዘብ ግብይቶችን አይፈጽሙ በህዝብ ዋይፋይ ላይ ሆነው ወደ ባንክ አፕሊኬሽንዎ አይግቡ ወይም በክሬዲት ካርድ ግብይት አይፈጽሙ። ጠላፊዎች በዋይፋዩ በኩል የምታስገቡትን ማንኛውንም መረጃ በቀላሉ መጥለፍ ይችላሉ። የግድ መጠቀም ካለባችሁ የራሳችሁን የሞባይል ዳታ (Mobile Data) ተጠቀሙ። ​ 2. ቪፒኤን (VPN) መጠቀም ቪፒኤን መጠቀም የእርስዎን መረጃ ኮድ በማድረግ (Encrypt) ማንም ሰው እንዳያየው ይከላከላል። በህዝብ ዋይፋይ ሲጠቀሙ ሁልጊዜ አስተማማኝ የሆነ ቪፒኤን ማብራት መረጃዎ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያደርጋል። ይህ በጣም  ቀላሉና ጠቃሚ ነገር  ነው ። ​ 3. "Auto-Join" የሚለውን ያጥፉ ስልካችን በራሱ ከማንኛውም ክፍት ዋይፋይ ጋር እንዲገናኝ ማድረግ አደገኛ ነው። ጠላፊዎች የካፌውን ዋይፋይ የሚመስል የሀሰት ዋይፋይ ሊፈጥሩ ስለሚችሉ፣ ሁልጊዜ ስልካችሁን በራሳችሁ ፍቃድ ብቻ ከዋይፋይ ጋር እንዲገናኝ አድርጉ (Turn off Auto-Connect)። ​ ማጠቃለያ ነፃ ዋይፋይ ሲያገኙ ከመገናኘታችሁ በፊት ደህንነታችሁን አስቡ። ይህ መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲደርስ ሼር ያድርጉት።