ልጥፎች

ልጥፎችን ከመለያ mobile care ጋር በማሳየት ላይ

ስልካችንን ቻርጅ ስናደርግ የምንሰራቸውና ባትሪ የሚያበላሹ 3 ትልልቅ ስህተቶች ​

ምስል
  ​ መግቢያ ሳላም የTechmedrek ቤተሰቦች ዛሬም እንደተለመደው  ቆንጆ  መረጃ ይዤ መጥቻለሁ እስከ መጨረሻ  ተከታተሉን ። የአንድ ስልክ ዕድሜ የሚወሰነው በባትሪው ጥንካሬ ነው። ብዙ ጊዜ ሳናውቀው የምንሰራቸው ጥቃቅን ስህተቶች የስልካችንን ባትሪ ቶሎ እንዲሞትና ቻርጅ እንዳይዝ ያደርጉታል። ባትሪችን ረጅም ዘመን እንዲኖር ከእነዚህ ስህተቶች እንቆጠብ። ​ 1. ስልኩ 100% እስኪሞላ መጠበቅ እና ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ላይ መተው ብዙዎቻችን ስልካችን 100% ሲሞላ ደስ ይለናል፤ ነገር ግን ሊቲየም-አዮን (Lithium-ion) ባትሪዎች መጨረሻ ደረጃ ላይ ሲደርሱ ከፍተኛ ጫና ይፈጠርባቸዋል። ስልካችንን ሁልጊዜ ከ 20% እስከ 80% ባለው ክልል ውስጥ ማቆየት ለባትሪው ጤንነት ተስማሚ ነው። እንዲሁም ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ላይ ሰክቶ መተው ስልኩ እንዲሞቅና ባትሪው እንዲያብጥ ያደርጋል። ​ 2. ቻርጅ እየተደረገ ስልክ መጠቀም (በተለይ ጌም እና ቪዲዮ) ስልካችን ቻርጅ እየሆነ ሲጠቀም (በተለይ ሶሻል ሚዲያ ስናይ፣ ቪዲዮ ስንከፍት ወይም ጌም ስንጫወት) ስልኩ በአንድ ጊዜ ሁለት ከባድ ስራ እየሰራ ስለሚሆን በጣም ይገላል። ይህ ሙቀት ደግሞ የባትሪውን ዕድሜ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳጥረዋል። ​ 3. የሌላ ስልክ ቻርጀር ወይም ርካሽ (Fake) ቻርጀር መጠቀም እያንዳንዱ ስልክ የሚፈልገው የኤሌክትሪክ ፍሰት (Voltage/Wattage) የተለያየ ነው። ከስልካችን ጋር የመጣውን ኦሪጅናል ቻርጀር ካጣን፣ በጥራት የተሰራና ለስልካችን የሚመጥን ቮልቴጅ ያለው መምረጥ አለብን። ዝም ብለን ያገኘነውን ርካሽ ቻርጀር መሰካት ባትሪውን በቀላሉ ያበላሸዋል። ​ ማጠቃለያ የስልክዎን ባትሪ ዕድሜ ለማራዘም ቻርጅ አጠቃቀምዎ ላይ ጥንቃቄ ያድርጉ።