ስልክዎ ከመጠን በላይ ይሞቃል? ምክንያቶቹ እና 5 መፍትሄዎች
መግቢያ
ስላም የtech medrek ቤተሰብ የዛሬ መረጃ በጣም ቀላልና ለስልካችን ግን እጅግ በጣም ጠቃሚ ነገር ነው።
የስልካችን መሞቅ (Overheating) ባትሪውን ከማዳከሙም ባለፈ የስልኩን እድሜ ያሳጥረዋል። ስልካችን ለምን ይሞቃል? በቀላሉስ እንዴት ማቀዝቀዝ እንችላለን? ዛሬ መፍትሄዎቹን ይዘንላችሁ ቀርበናል።
1. ከባድ መተግበሪያዎችን (Apps) ለረጅም ጊዜ መጠቀም
ከፍተኛ ግራፊክስ ያላቸውን ጌሞች መጫወት ወይም ቪዲዮ ኤዲቲንግ አፖችን ለረጅም ሰዓት መጠቀም ፕሮሰሰሩ ላይ ጫና ስለሚፈጥር ስልኩ እንዲሞቅ ያደርጋል። አልፎ አልፎ ስልኩን ማሳረፍ ተገቢ ነው።
2. ቻርጅ እያደረጉ ስልክ መጠቀም
ስልክ ቻርጅ በሚደረግበት ወቅት ባትሪው ሙቀት ያመነጫል። በዚህ ሰዓት ተጨማሪ ስራዎችን (ለምሳሌ Game ቪዲዮ ማየት) መስራት ሙቀቱን በእጥፍ ይጨምረዋል። ይህ ለባትሪ ደህንነት አደገኛ ነው።
3. አላስፈላጊ የሆኑ ኮኔክሽኖችን ማብራት
ዋይፋይ (Wi-Fi)፣ ብሉቱዝ (Bluetooth) እና ጂፒኤስ (GPS) ባንፈልጋቸውም እንኳ ክፍት ሆነው ሲቀሩ ስልኩ ሲግናል ለመፈለግ በሚያደርገው ጥረት ሙቀት ይፈጥራል። ካልፈለግናቸው ብንዘጋቸው ይመከራል።
4. የስልኩን ከቨር (Case) ለጥቂት ጊዜ ማውለቅ
አንዳንድ ወፍራም የስልክ ከቨሮች ሙቀት ወደ ውጭ እንዳይወጣ ያደርጋሉ። ስልኩ በጣም መሞቅ ሲጀምር ከቨሩን በማውለቅ አየር እንዲያገኝ ወይም እንዲቀዘቅዝ ማድረግ ፍቱን መፍትሄ ነው።
5. ሲስተም አፕዴት (System Update) ማድረግ
አንዳንድ ጊዜ ስልኩ የሚሞቀው በሶፍትዌር ችግር ሊሆን ይችላል። የቅርብ ጊዜውን አፕዴት ማድረግ ወይም software ማሳደስ እነዚህን ችግሮች ሊቀርፍ ይችላል።
ማጠቃለያ
ስልክዎ ሲሞቅ ዝም ብለው አይለፉት፤ ከላይ ያሉትን መፍትሄዎች በመጠቀም ደህንነቱን ይጠብቁ። የእርስዎ ስልክ እንዲህ አይነት ችግር አጋጥሞት ያውቃል?

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ