ስልካችንን ስንገዛ Original (ዋናው) መሆኑን በ 2 ደቂቃ ውስጥ የምናረጋግጥበት ቀላሉ መንገድ

 



መግቢያ 

ሳላም የTechmedrek ቤተሰቦች በዛሬ መረጃችን አዲስም ሆነ ያገላገለ ስልክ ስንገዛ ማድረግ ያለብንን  ጥንቃቄዎች  እናያለን ።

በአሁኑ ሰዓት በገበያ ላይ ኦሪጅናል የሚመስሉ ነገር ግን የፎርጅድ (Copy) ስልኮች በጣም በዝተዋል። ከፍተኛ ብር አውጥተን የገዛነው ስልክ ትክክለኛ መሆኑን እንዴት በቀላሉ ማወቅ እንችላለን? መልሱ እጅግ ቀላል ነው፤ የ IMEI ቁጥርን መጠቀም።

1. የ IMEI ቁጥርን ማግኘት

በማንኛውም ስልክ ላይ የስልክ መደወያውን በመክፈት *#06# ብለው ሲደውሉ ባለ 15 አሃዝ የ IMEI ቁጥር ይመጣልዎታል። ይህንን ቁጥር ስክሪንሹት ያድርጉት ወይም ወረቀት ላይ ይጻፉት።

2. በ imei.info ድረ-ገጽ ማረጋገጥ

የመቶ ዓመት ዕድሜ ባለው ስማርትፎንዎ ላይ ኢንተርኔት በመክፈት ወደ www.imei.info ድረ-ገጽ ይግቡ። የጻፉትን 15 አሃዝ ቁጥር እዚያ ላይ አስገብተው "Check" የሚለውን ይጫኑ።

3. ውጤቱን ማወዳደር

ድረ-ገጹ የስልኩን ትክክለኛ ሞዴል፣ የተመረተበትን ኩባንያ (Samsung, iPhone, Techno ወዘተ) እና ዝርዝር መረጃዎችን ያሳየዎታል። በእጅዎ ያለው ስልክ እና ድረ-ገጹ ላይ የመጣው መረጃ ፍጹም አንድ አይነት ካልሆነ ስልኩ ፎርጅድ ወይም የተቀየረ መሆኑን በቀላሉ ማወቅ ይችላሉ።

ማጠቃለያ

አዲስም ሆነ ያገለገለ ስልክ ከመግዛትዎ በፊት ይህንን ቀላል ፍተሻ በማድረግ ራስዎን ከኪሳራ ይጠብቁ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በ2026፦ ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ እየቀየሩ ያሉ 3 አስደናቂ ነገሮች

ስለ ዋትስአፕ (WhatsApp) የማታውቋቸው 4 አስገራሚ ድብቅ ጥቅሞች

ስልክዎ ከመጠን በላይ ይሞቃል? ምክንያቶቹ እና 5 መፍትሄዎች