በስልካችን ኢንተርኔት (Data) ቶሎ እንዳያልቅብን ምን እናድርግ
መግቢያ
ሳላም! የTechmedrek ቤተሰብ ዛሬ አርብ ሜይ 15 ነው በአሁኑ ሰዓት በጣም ጠቃሚ የሆነ ርዕስ መርጫለሁ
እስከ መጨረሻ ተከታተሉን ።
እስከ መጨረሻ ተከታተሉን ።
የኢንተርኔት ዳታ ዋጋ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ የገዛነው ጥቅል ሳይታወቅ ቶሎ ማለቁ ትልቅ ችግር ነው። ነገር ግን ጥቂት ቅንብሮችን በማስተካከል ዳታችንን መቆጠብ እንችላለን።
1. አውቶማቲክ አፕዴት (Auto-update) ማቆም
Play Store ውስጥ በመግባት Settings > Network Preferences > Auto-update apps የሚለውን "Over Wi-Fi only" ወይም "Don't auto-update" ማድረግ። ይህ ስልካችን እኛ ሳናውቅ ጥቅል እንዳይበላ ይረዳል።
2. ዳታ ሴቨር (Data Saver) ማብራት
በስልካችን Settings > Connections > Data Usage ውስጥ በመግባት "Data Saver" የሚለውን ማብራት። ይህ ከጀርባ (Background) ዳታ የሚበሉ አፖችን ይገድባል።
3. የማህበራዊ ሚዲያ ቅንብሮች
- TikTok/YouTube: ቪዲዮዎች በጥራት (HD) ፋንታ "Data Saver" ሞድ ላይ እንዲሆኑ ማድረግ።
- Telegram/WhatsApp: ፎቶዎችና ቪዲዮዎች ያለ እኛ ፍቃድ (Auto-download) እንዳይወርዱ ማስተካከል።
ማጠቃለያ
እነዚህን ቀላል መንገዶች በመጠቀም የገዙትን ጥቅል ለረጅም ጊዜ መጠቀም ይችላሉ። ይህ መረጃ ለሌሎች እንዲደርስ ለጓደኞችዎ ያጋሩ።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ