የፌስቡክ (Facebook) አካውንታችን እንዳይጠለፍ ማድረግ ያለብን 3 ወሳኝ ነገሮች
መግቢያ
ፌስቡክ የብዙዎቻችን የዕለት ተዕለት የመረጃ መለዋወጫ ሆኗል። ነገር ግን የአካውንታችን ደህንነት ካልተጠበቀ የግል ምስሎቻችን እና መረጃዎቻችን ለሌቦች ሊጋለጡ ይችላሉ። ዛሬ አካውንታችንን አስተማማኝ የምናደርግባቸውን 3 ቀላል መንገዶች እናያለን።
1. የሁለትዮሽ ማረጋገጫ (Two-Factor Authentication) ማብራት ይሄ በጣም ወሳን ነገር ነው። ይህን ነገር በማስተካከል ብቻ የግል መረጃዎቻችን ከሌቦች መጠበቅ እንችላለን ማለት ነው።
ይህ በጣም አስፈላጊው ጥንቃቄ ነው። ይህንን ካበራን በኋላ፣ ሌላ ሰው የእኛን ፓስወርድ ቢያውቅ እንኳ ወደ አካውንታችን ለመግባት ወደ ስልካችን የሚላክ አጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) ኮድ ይጠይቃል።
- እንዴት ይበራል? Settings > Security and Login > Use two-factor authentication የሚለውን በመጫን ማብራት ይቻላል።
2. አጠራጣሪ የሆኑ "ሊንኮችን" (Links) አለመንካት
"ማን ፕሮፋይልህን አየ?" ወይም "ይህ ቪዲዮ አንተ ነህ?" የሚሉ መልዕክቶች በMessenger ወይም በPost ሲመጡልህ በፍጹም አትንካ። እነዚህ ሊንኮች ያንተን ፓስወርድ ለመስረቅ የተዘጋጁ ወጥመዶች ናቸው።
3. ንቁ የሆኑ መሣሪያዎችን (Active Sessions) መከታተል
አካውንትህ በሌላ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ተከፍቶ እንደሆነ ሁልጊዜ አረጋግጥ።
- ለማረጋገጥ፦ Settings > Security and Login > Where You're Logged In የሚለው ስር በመግባት የማታውቀው ስልክ ካለ "Log Out" በማድረግ ማስወጣት ትችላለህ።
ማጠቃለያ
የሶሻል ሚዲያ ደህንነታችንን መጠበቅ የራሳችን ኃላፊነት ነው። እነዚህን 3 ነጥቦች ዛሬውኑ በመተግበር አካውንታችሁን ጠብቁ። እናንተስ ፌስቡካችሁ ተጠልፎባችሁ ያውቃል? ምን አደረጋችሁ? በኮሜንት አጋሩን።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ