የስልክዎን ኢንተርኔት ፍጥነት ለመጨመር የሚረዱ 4 ቀላል ዘዴዎች
መግቢያ
ኢንተርኔት እየተጠቀሙ እያለ መቆራረጥ ወይም መዘግየት በጣም ያበሳጫል። ብዙ ጊዜ ችግሩ ከኔትወርክ ሰጪ ድርጅቱ (ከቴሌ) ብቻ ሳይሆን በስልካችን ውስጥ ካሉ አንዳንድ ቅንብሮች (Settings) ሊሆን ይችላል። ዛሬ የስልክዎን ኢንተርኔት ፈጣን ለማድረግ የሚረዱ 4 ዘዴዎችን እናያለን:: በቀላሉ እነዚህን ቅንብሮች(settings) በማስተካከል ብቻ የስልካችን network የተሻለ ማድረግ እንችላለን ማለት ነዉ ።
1. "Background Data" መዝጋት
ስልካችን ውስጥ ያሉ አፖች እኛ ባንጠቀማቸውም እንኳ ከበስተጀርባ ኢንተርኔት ይበላሉ። ይህ ደግሞ ለምንጠቀመው አፕ የሚደርሰውን ፍጥነት ይቀንሰዋል።
- መፍትሄ፦ Settings > Apps ውስጥ በመግባት የማንጠቀማቸው አፖች "Background Data" እንዳይጠቀሙ መዝጋት።
2. የብሮውዘር (Browser) ዳታ ማጽዳት
እንደ Chrome ያሉ ብሮውዘሮችን በምንጠቀምበት ጊዜ "Cache" የሚባሉ ብዙ ፋይሎችን ያስቀምጣሉ። እነዚህ ፋይሎች ሲበዙ ብሮውዘሩ እንዲዘገይ ያደርጉታል።
- መፍትሄ፦ በChrome Setting ውስጥ በመግባት "Clear browsing data" የሚለውን ይጫኑ።
3. "Network Settings" እንደገና ማስተካከል (Reset)
አንዳንዴ ኔትወርኩ በጣም ከዘገየ በስልካችን ውስጥ ያለውን የኔትወርክ ቅንብር ወደ ነበረበት መመለስ ትልቅ ለውጥ ያመጣል።
- መፍትሄ፦ Settings > General Management > Reset > Reset Network Settings። (ይህ ሲደረግ ዋይፋይና ብሉቱዝ ድጋሚ ኮኔክት መደረግ አለባቸው)።
4. 4G/5G ብቻ እንዲሆን ማድረግ
ስልካችን ኔትወርክ ሲዳከም በራሱ ወደ 3G ወይም 2G ሊቀየር ይችላል። ይህ እንዳይሆን "Preferred network type" የሚለውን 4G ወይም 5G ላይ ብቻ ማድረግ ፍጥነቱ እንዳይቀንስ ይረዳል ።
ይህ automatical የሚቀያየር ከሆነ ማለትም ከ2G/3G network ወደ 4G/5G በራሱ ጊዜ የሚቀያየር ከፍ ብሎ ዝቅ በምልበት ጊዜ network ይቆረጣል ማለት ነው።
ማጠቃለያ
እነዚህን ዘዴዎች ሞክረው ኢንተርኔትዎ ላይ ለውጥ ካዩ ለጓደኞችዎ ሼር ያድርጉላቸው። የእርስዎ ኢንተርኔት ፍጥነት አሁን እንዴት ነው?

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ