አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ምንድን ነው? ለሕይወታችንስ ያለው ጥቅም
መግቢያ
በአሁኑ ጊዜ "AI" ወይም "አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ" የሚለውን ቃል በየቦታው እንሰማለን። ብዙዎቻችን ስለ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ስናስብ ወደ አእምሯችን የሚመጣው እንደ ሰው የሚናገሩ ሮቦቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን AI ከዚያ ያለፈና በየቀኑ በስልካችንና በኮምፒውተራችን የምንጠቀመው ረቂቅ ቴክኖሎጂ ነው።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ምንድን ነው?
በአጭሩ AI ማለት ማሽኖች ወይም ኮምፒውተሮች እንደ ሰው እንዲያስቡ፣ እንዲማሩ እና ችግሮችን እንዲፈቱ ተደርገው የሚሰሩበት የቴክኖሎጂ ዘርፍ ነው። ስልካችን የሰውን ድምፅ ለይቶ እንዲያውቅ፣ ፌስቡክ እኛ የምንደሰትበትን ቪዲዮ መርጦ እንዲያሳየን ወይም በራሳቸው የሚነዱ መኪኖች እንዲመረት የሚያደርገው ይሄው AI ነው። ከዚያም ባለፈ አና ሰዎች የሚንሠራቸውን ሥራ ተክቶ የመሥራት ችሎታ ያላቸው ቴክኖሎጅዎች ናቸው ።
AI በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ
- የድምፅ ረዳቶች፦ እንደ Google Assistant ያሉ አፖች የምንለውን ሰምተው መልስ የሚሰጡን በAI አማካኝነት ነው።
- ትርጉም (Translation)፦ ጎግል ትርጉም (Google Translate) አንድን ቋንቋ ወደ ሌላ የሚቀይረው የቃላትን ፍቺ በAI አጥንቶ ነው።
- ፎቶግራፍ፦ የስልካችን ካሜራ የሰውን ፊት ለይቶ ጥራቱን የሚያስተካክለውና መብራቱን የሚመጥነው በAI እርዳታ ነው።
የAI የወደፊት ጉዞ
ወደፊት AI በሕክምና (በሽታን አስቀድሞ በመለየት)፣ በትምህርት እና በሥራ ቦታዎች ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል። ስራችንን ለማቅለልና ፈጣን ለማድረግ AIን መልመድና ለበጎ ተግባር መጠቀም መጀመር ለሁላችንም ይጠቅማል።
ማጠቃለያ
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስራችንን የሚያቀልልልንና አዳዲስ ፈጠራዎችን እንድንፈጥር የሚረዳን ታላቅ መሣሪያ ነው። እናንተስ AIን ለምን ተግባር ትጠቀሙበታላችሁ? ቻት ጂፒቲን (ChatGPT) ሞክራችሁት ታውቃላችሁ? አስተያየታችሁን በኮመንት አጋሩን።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ