የሶሻል ሚዲያ አካውንትዎን ከጠላፊዎች (Hackers) ለመጠበቅ የሚረዱ 4 መንገዶች
መግቢያ
በአሁኑ ጊዜ የፌስቡክ፣ የቴሌግራም ወይም የኢሜል አካውንታችን መጠለፍ ትልቅ ስጋት እየሆነ መጥቷል። ጠላፊዎች የግል መረጃዎቻችንን በመውሰድ ለተለያዩ መጥፎ ተግባራት ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። ዛሬ አካውንታችንን ይበልጥ ጠንካራ እና አስተማማኝ ለማድረግ የሚረዱ 4 ቀላል ግን ወሳኝ መንገዶችን እናያለን።
1. ጠንካራ የይለፍ ቃል (Strong Password) መጠቀም
ብዙዎቻችን በቀላሉ የሚገመቱ የይለፍ ቃሎችን (ለምሳሌ፦ ስማችንን ወይም ስልክ ቁጥራችንን) እንጠቀማለን። ይህ ለጠላፊዎች ትልቅ እድል ይሰጣል። ይልቁንም ቁጥሮችን፣ ምልክቶችን (@, #, $) እና ትላልቅና ትናንሽ ፊደላትን የቀላቀለ የይለፍ ቃል መጠቀም ይኖርብናል።
2. ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Factor Authentication - 2FA) ማብራት
ይህ ዘዴ አካውንታችሁን ለመጠበቅ በጣም አስተማማኝ ነው። ይህ ሲበራ አንድ ሰው የይለፍ ቃላችሁን ቢያውቅ እንኳን፣ ወደ ስልካችሁ የሚላከውን ሚስጥራዊ ኮድ ሳያስገባ መግባት ወይንም በቀላሉ መክፈት አይችልም። በፌስቡክ፣ በቴሌግራም እና በኢሜል ሴቲንግ ውስጥ በመግባት ይህንን ማብራት ትችላላችሁ።
3. አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመንካት (Avoid Phishing)
"ሎተሪ ደርሶዎታል" ወይም "ይህ ቪዲዮ የእርስዎ ነው?" የሚሉ አሳሳች መልዕክቶች ከማይታወቁ ሰዎች ሊላኩላችሁ ይችላሉ። እነዚህን ሊንኮች ስትነኩ የይለፍ ቃላችሁን እንድታስገቡ ሊጠይቋችሁ ይችላሉ። በፍጹም እንደዚህ ያሉ ሊንኮችን አትንኩ! ይህ በጣም ጥንቃቄ የሚያስፈልግ ነገር ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ማለት ነው ።
4. የስልክ ሶፍትዌርን በየጊዜው ማደስ (Update)
የስልካችን ወይም የምንጠቀማቸው አፖች አዲስ ማሻሻያ (Update) ሲመጣላቸው ወዲያውኑ መጫን አለብን። እነዚህ ማሻሻያዎች ከዚህ በፊት የነበሩ የደህንነት ክፍተቶችን በመድፈን ለጠላፊዎች አስቸጋሪ ያደርጉባቸዋል። የተላያዩ አዲስ ነገር ወይንም ማሻሻያ ይዞ ስለሚመጡ በየጊዜው update በማድረግ ከእንግዲህ አይነት አደጋ ወይንም ሌብነት በቀላሉ ማትረፍ እንችላለን ።
ማጠቃለያ
የሶሻል ሚዲያ ደህንነትን መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው። አካውንትዎ ተጠልፎ ያውቃል? ወይም የጠለፋ ሙከራ ተደርጎብዎታል? ተሞክሮዎን በኮመንት ያጋሩን።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ