አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በ2026፦ ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ እየቀየሩ ያሉ 3 አስደናቂ ነገሮች
መግቢያ ሳላም እንዴት ናችሁ የTech medrek ቤተሰቦች ዛሬ ይዤላችሁ የመጣሁት መረጃ ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ እየቀየሩ ያሉ 3 አስደናቂ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እናያለን ። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ገና ወደፊት ይመጣል የምንለው ቴክኖሎጂ መሆኑ አብቅቷል። አሁን በደረስንበት በ2026 ዓ.ም AI ከምንገምተው በላይ ፈጣን በሆነ ሁኔታ የዕለት ተዕለት ሕይወታችንን፣ አሠራራችንን እና የፈጠራ ዓለምን እየቀየረው ይገኛል። ቀደም ሲል AI ጽሁፍ ለመጻፍ ወይም ቀላል ጥያቄዎችን ለመመለስ ብቻ የምንጠቀምበት ይመስለን ነበር፤ አሁን ግን ነገሮች ሙሉ በሙሉ ተቀይረዋል። በዚህ ጽሁፍ በ2026 ዓ.ም ዓለማችንን በከፍተኛ ሁኔታ እያስገረሙ ያሉ 3 የ-AI አብዮቶችን እንመለከታለን። 1. የቪዲዮ እና የፎቶ ፈጠራ (Generative AI Video) በአሁኑ ወቅት ማንም ሰው ምንም ዓይነት ካሜራ ወይም ስቱዲዮ ሳይኖረው፣ በጽሁፍ ትዕዛዝ (Prompt) ብቻ እውነተኛ የሚመስሉ እጅግ ጥራት ያላቸውን ቪዲዮዎች እና ፎቶዎችን በ-AI መፍጠር ይችላል። ይህ የፊልም ኢንዱስትሪውን፣ የማስታወቂያ ሥራዎችን እና የሶሻል ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎችን (Content Creators) ሥራ በእጅጉ አቅልሏል። ከአንድ ጽሁፍ ተነስተው ሙሉ ታሪክ ያላቸውን ተንቀሳቃሽ ምስሎች መሥራት አሁን እውን ሆኗል። 2. የሰዎች የዕለት ተዕለት ረዳቶች (Advanced AI Assistants) አሁን ላይ ያሉ የ-AI ረዳቶች ልክ እንደ እውነተኛ የሰው ልጅ ማሰብ፣ ስሜትን መረዳት እና ድምፅን ለይተው ማውራት የሚችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። በስልካችን ወይም በኮምፒውተራችን ላይ ያሉ የ-AI ረዳቶች የዕለቱን ፕሮግራማችንን ከማስተካከል ጀምሮ፣ ውስ...